ለወሰን የለሽ የክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር በጋምቤላ ክልል የተገኘው የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ በዛሬው እለትም በንዌር ዞን ጅካው ወረዳ በመገኘት ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ለወሰን የለሽ የክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር በጋምቤላ ክልል የተገኘው የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ በዛሬው እለትም በንዌር ዞን ጅካው ወረዳ በመገኘት ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
በፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት መለሰ አባተ እንደተናገሩት ኢትዮጵያውያን በርካታ መልካም እሴቶች ያሏት ሀገር በመሆኗ እነዚህን እሴቶች መንከባከብ እንደሚገባ በመግለጽ የአብሮነት፣የመደጋገፍና የትብብር እሴቶች በበጎ ፍቃድ ተግባራት እየተጠናከሩ መምጣታቸውን ገልጸዋል።
ሀገራችን በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤቶ እያመጣች ሲሆን ይኸም የማንሰራራት ዘመን ማሳያ በመሆኑ ወጣቱ የጀመረውን ሁሉንአቀፍ ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የንዌር ብሄረሰብ ዞን አመራሮች፤ወጣቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተው የአዲስአበባ ከተማ ወጣቶች ክንፍ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። More..
መጪዎቹ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች የዜግነት ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡
መጪዎቹ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች የዜግነት ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡
የመስቀልና ኢሬቻ በዓላትን አከባበር አስመልክቶ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ጋር በተካሄደው ውይይት ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ ባስተላለፉት መልዕክት የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች በሰላም፣ በልማት እና በመልካም አስተዳደር መስኮች ባለፉት የለውጥ ዓመታት አንጸባራቂ ስኬት ያስመዘገቡ ሥራዎችን ማከናወናቸውን አውስተዋል፡፡ “የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የምናከብረው ሀገራችን የዘመናት ቁጭታችን የነበረውን በተፈጥሮ ሀብታችን የመጠቀምና የመልማት ጥያቄያችንን የመለሰውን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አጠናቃ ባስመረቀችበት ማግሥት ነው” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ቅርስ የሆኑትን በዓላት በከፍተኛ ድምቀትና በሰላማዊ ድባብ ለማክበር በሚደረገው እንቅስቃሴ የክፍለ ከተማው ወጣቶች ባለቤትና ንቁ ተሳታፊ በመሆን እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ በንቃት በመሳተፍ የዜግነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌትነት ዓይናለም በበኩላቸው የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ከፍተኛ ደረጃ እንዲኖራት ያደረጉ ታላላቅ ቅርሶች መሆናቸውን አውስተው፣ የዘንድሮዎቹ በዓላት እንደሀገር ድርብ ድል በተመዘገበበት ወቅት የሚከበሩ በመሆናቸው ጸረ ሰላም ኃይሎች የከሰረ የፖለቲካ አጀንዳቸውን በበዓላቱ ወቅት ለማስፈጸም የሚያደርጉትን ጥረት በማክሸፍ ረገድ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች የሰላም ዘብ በመሆን በላቀ ድምቀት እንዲከበር ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉ የክፍለ ከተማው ወጣቶች በሰጡት አስተያየት የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት የመላው ኢትዮጵያዊያን የጋራ በዓላት መሆናቸውን ገልጸው፣ በዓላቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በንቃት በመሳተፍ ድርሻቸውን እንደሚያበረክቱ አመልክተዋል፡፡ የወጣቶች የነቃ ተሳትፎ በሁሉም መስኮች በክፍለ ከተማው ለተመዘገበው ስኬት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ያመለከቱት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም አሰፋ፣ በዓላቱን የጸረ ሰላም አጀንዳ ማስፈጸሚያ ለማድረግ የሚፍጨረጨሩ ኃይሎች ዓላማቸው እንዳይሳካ ከወጣቶች ከፍ ያለ ኃላፊነት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ወጣቶች በዓላቱ በሰላም እንዲከበሩ ለማድረግ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ በየወረዳዎቻቸው ውይይት ማድረጋቸውን የተናገረችው የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ ወጣት ሄለን ለገሠ፣ በክፍለ ከተማው የተካሄደው የማጠቃለያ መድረክ መጪዎቹ በዓላት በደመቀና ሰላማዊ በሆነ አግባብ እንዲከበር ግንባር ቀደም በመሆን ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን አስታውቃለች፡፡
መስከረም 11/2018
ሀገሬን እገነባለሁ ኃላፊነቴንም እወጣለሁ!"
ሀገሬን እገነባለሁ ኃላፊነቴንም እወጣለሁ!"
በኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር እና በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት ከብሎክ ጀምሮ በሀገራዊ ሰላም እና ልማት ላይ ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የወጣቶች መድረክ በአዲስ አበባ ደረጃ ሀገራዊና ከተማዊ ሰላምን ማፅናት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተግባቦት በመፍጠር ተጠቃሏል።
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ የወጣት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው የወጣቱን ዕምቅ አቅም በመጠቀም ሁለንተናዊ ብልፅግናን በማረጋገጥ ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆኑ የዛሬም ሀገር ወራሽ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ህብረ ብሔራዊቷ የሁላችን ከተማ አዲስ አበባ ስሟንና ክብሯን በማይመጥን ጉስቁልና ውስጥ መቆየቷን የጠቀሱት ዶ/ር ከይረዲን ወጣቱንም ታሳቢ በማድረግ እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከሩን መመልከታቸውን አስረድተዋል።
በሰላም ሰራዊት እና በሌሎችም ህዝብ እና መንግስት ተቀናጅተው ያከናወኗቸው ተግባራት አስደናቂ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በህብረብሔራዊነት ደምቀን አንድነታችንን ማጠናከር ይጠበቅብናል የሚል መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል።
ሀገር ከግል እና ከቡድን ጥቅም በላይ መሆኗን በመረዳት በሀገር ጉዳይ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንደሚገባ ያመላከቱት ዶ/ር ከይረዲን በምክክር ኮሚሽኑ ያልተነሳ አጀንዳ ስለሌለ ሲንከባለሉ የቆዩ ችግሮች ሁሉ መፍትሄ እንደሚያገኙ ያላቸውን ፅኑ ዕምነትም ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በርካታ ተግዳሮቶችን ተሻግራ ተስፋዋን እያለመለመች ያለች ሀገር መሆኗን የጠቆሙት ዶ/ር ከይረዲን የሰላም እሴት ግንባታችን አጠናክረን ማስቀጠል ይገባናል ብለዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ወጣት ፈዲላ ቢያ የትናንት ወጣቶች የዛሬ አባቶች የህይወት መስዋዕነትነት ከፍለው ሉዓላዊት ሀገር ማውረሳቸውን ጠቅሰው በደም የተከበረችውን ሀገር በላብ ማፅናት የህይወት መስዋዕትነት ባይጠይቅም ላቅ ያለ ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ መረዳት ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ወጣት ለሰላሙም ለልማቱም ጉልህ አሻራውን እያሳረፈ እንደሚገኝ የገለፁት ወጣት ፈዲላ የሀገራችንን ሰላም ለማደፍረስ አዲስ አበባን ለማወክ እንቅልፍ አጥተው የሚሰሩ በመኖራቸው ለአስተማማኝ እና ለዘላቂ ሰላም በላቀ ቁርጠኝነት መረባረብ እንደሚጠበቅም አስረድተዋል።
ፅንፈኛ አካላት ዜጎች በሀገራቸው ተስፋ እንዲቆርጡ ፣ የመጣውን ተጨባጭ ለውጥ እንዳይመለከቱ በትኩረት እንደሚሰሩ ያስገነዘቡት ወጣት ፈዲላ የጫካ ትግላቸው እንደማያዋጣ ሲመለከቱ በሚዲያ ላይ እየዘመቱ በመሆኑ ፅንፈኝነታቸውን ማጋለጥና ሚዲያን ለበጎ ዓላማ መጠቀምን ማጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል።
ወጣቶች ጉልህ አሻራቸውን እያሳረፉበት ለሚገኘው ልማት እንዲሁም የኑሮ ውድነትን ጫና ለማቃለል እየተከናወኑ ለሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተገቢውን የሚዲያ ሽፋን በመስጠት ማስፋት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የሚነሱ ጥያቄዎችን የዕቅድ አካል በማድረግ የጋራ ጥረት እንደሚደረግ የገለፁት ወጣት ፈዲላ ሰላም ሚኒስቴርም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ወጣቶች በጋራ እንዲመክሩ የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ወጣት መለሰ አባተ ባቀረቡት የውይይት መነሻ ሰነድ የሀገር ብልፅግና የሚረጋገጠው በወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ መሆኑንና ኢትዮጵያ አሁን ለደረሰችበት ተስፋ ሰጪ ለውጥም የበኩላቸውን ሲወጡ መቆየታቸውን አውስተዋል።
ምክንያታዊነትን መላበስ ፣ ሀገራዊ ጥቅምን ማስቀደም ፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ማጠናከር፣ በብዝሀነት የሚፀና አንድነት ማሳደግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
አወንታዊ ሰላም የግጭት እና የጦርነት አለመኖር ብቻ ሳይሆን ፍትህ ፣ እኩልነት እና ደህንነት መሆኑን የጠቆሙት ወጣት መለሰ የሰላም ግንባታ ግጭትን ከመፍታት ባሻገር ግጭት እንዳይፈጠር ቀድሞ መከላከል መሆኑንም አስረድተዋል።
ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጠቀሱት ወጣት መለሰ ለዘላቂ ተጠቃሚነት በከተማችን እየተገነቡ የሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶችም የወጣቶችን ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ለከተማችን እና ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲሁም ለወጣቶች ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት የድርሻቸውን መወጣቸውን እንደሚያጠናክሩ የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች ገልፀዋል።
https://www.facebook.com/share/1AbCJ1PNn1/
የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የተከናወኑ የተሞክሮ ስራዎችን ተዘዋውረው ተመለከቱ
የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ከበጀት አመቱ 9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ጎን ለጎን በቦሌ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የተከናወኑ የተሞክሮ ስራዎችን ተዘዋውረው በመመልከት ልምድ ተለዋውጠዋል።
በተሞክሮ ምልከታው የወጣቶች ስራ ዕድል ተጠቃሚነት ፣ የሌማት ቱሩፋት ተግባራትና በፓርቲ መዋቅር የተከናወኑ የቴክኖሎጂ ማበልጸግ ስራዎች ተዳሰዋል!
በምልከታው የፌዴራል ዋና ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ አመራሮች እና የክልሎች የክንፉ አመራሮች ተሳትፈውበታል!
የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አመራሮች በቦሌ ክፍለ ከተማ ጉብኝት አደረጉ፡፡
በብልጽግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት አባንግ ኩመዳን የተመራው የወጣቶች ክንፍ አመራሮች ቡድን በቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ የሥራ እንቅስቃሴ እንዲሁም በክፍለ ከተማው የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ እንቅስቃሴዎችና ፕሮጀክቶችን ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን፣ ስለተግባራቱ አፈጻጸምም ገለፃ ተደርጎለታል፡፡ የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባልና የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው በጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት ክፍለ ከተማው ወጣቶች ሁለንተናዊ ብልጽግናን ዕውን ለማድረግ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራሪ ዘርፎች ተሳታፊነታቸውንና ተጠቃሚነታቸውን የሚያሳድጉ ተግባራትን በስፋት ያከናወነ ሲሆን፣ ወጣቶች ለክፍለ ከተማው ብሎም ለአዲስ አበባ ሰላምና ልማት እያበረከቱ ያለው አስተዋጽኦ በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ተናግረዋል፡፡ ክፍለ ከተማው በሁሉም መስኮች ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ላስመዘገበው አንጸባራቂ ስኬት የወጣቶች ሚና ከፍተኛ እንደነበር ያወሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አመራሮች በክፈለ ከተማው ያደረጉት ጉብኝት ጠቃሚ ልምዶችን በመለዋወጥ የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ከዳር እንዲደርስ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አክለው ገልጸዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት አባንግ ኩመዳን በበኩሏ የቦሌ ክፍለ ከተማ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚደነቅና በአርአያነት የሚወሰድ መሆኑን ገልጻ፣ የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅርንጫፍ የወጣቶችን አቅም ለብልጽግና ስኬት ለማዋል ያደረገው እንቅስቃሴና የተገኘው ውጤት አበረታች በመሆኑ የፓርቲው ወጣት ክንፍ አመራሮች በቀጣይ ለሚያከናውኑት እንቅስቃሴ ጠቃሚ ግብዓት ማግኘታቸውን ተናግራለች፡፡ ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የገለጹት የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ለማ፣ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አመራሮች በክፍለ ከተማው ጉብኝት ለማድረግና ልምድ ለመቅሰም በመምጣታቸው ምስጋና በማቅረብ ወጣቶች በሁሉም ዘርፍ ሚናቸው የበለጠ እንዲያድግ በክፍለ ከተማው የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በጉብኝቱ የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ይፋዊ ዌብሳይት ለእይታ በቅቷል፡፡
ሚያዚያ 17/2017
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፤
ትንሣኤ የመሥዋዕትነት፣ የጽናት እና የተስፋ በዓል ነው።
የበደለው ዓለም ነው። የተሠዋው ግን ክርስቶስ ነው። ያጠፋው የሰው ልጅ ነው፣ የካሠው ግን ክርስቶስ ነው። ባለ ዕዳው ሰው ነው። ከፋዩ ግን ክርስቶስ ነው።
የክርስቶስ ሞት አንድም ለማዳን ነው፤ አንድም ለትምህርት ነው። ስለ ብዙዎች ሲባል መሥዋዕትነት ካልተከፈለ ብዙዎችን ማዳን አይቻልም። ሀገርን፣ ሕዝብን፣ ወገንን ማዳን ከተፈለገ መሥዋዕትነት መክፈል ይገባል። ቃል ክርስቶስ በቃሉ ብቻ አልተናገረም። በመስቀል ላይ ውሎ ፍቅሩን በተግባር ገለጠው እንጂ። ራሱ አስታራቂ፣ ራሱ ታራቂ፣ ራሱም መሥዋዕት ሆነ።
ዛሬ ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ መሥዋዕት ለመሆን የተዘጋጀ መሆን አለበት። በሌሎች መሥዋዕትነት መጓዝ የኦሪት ሰዎችም አድርገውታል። ሺ በጎችንና ሺ ፍየሎችን ሠውተው ነበረ። አልሆነም እንጂ። ሀገርን ማዳን የሚቻለው ሌሎችን በመሠዋት አይደለም። ራስን በመሠዋት እንጂ። የራስን ጉልበት፣ ጊዜ እና ዕውቀት በመሠዋት እንጂ። የራስን ክብርና ኢጎ በመሠዋት እንጂ።
ሀገርን ለማዳን ወደ ትኅትና፣ ወደ ዕርቅ እና ወደ ምክክር መስቀል አውርዶ ራስን መሠዋት ያስፈልጋል። መስቀል መከራ ነው፤ ስድብ ነው፤ ግርፋት ነው፤ ውርደት ነው። ራሳችንን ለሰላምና ለዕርቅ መንገድ ስናዘጋጅ ከብዙዎች ዘንድ ስድብ፣ ርግማን፣ መከራ፣ ይጠብቀናል። የሚያዋጣን ግን ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ የኢትዮጵያን መስቀል መሸከም ነው። ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ስንል መስቀሏን መሸከም።
ትንሣኤ ከጽናት በኋላ የሚገኝ ድል ነው። ከፊቱ የጅምላ ፍርድ አለው፤ ከፊቱ ውግዘት አለው፤ ከፊቱ ግርፋት አለው፤ ከፊቱ መራቆት አለው፤ ከፊቱ መከዳት አለው፤ ከፊቱ የፀሐይ መጨለም፣ የጨረቃ ደም መልበስ፣ የከዋክብትም መርገፍ አለው። በዚህ ሁሉ ግን በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ክርስቶስ በጽናት ቆመ። ስለ ዓላማ ሲባል መከራን ታገሠ። ስለ ሰው ልጅ ሲባል ሁሉን እየቻለ በጽናት ተጓዘ።
ሀገር ጽናት ትፈልጋለች። በመከራዎች እና በውግዘቶች ፊት በጽናት መቆም። በስድብና በንቀት ፊት በጽናት መቆም። እንደ ፀሐይ የሚታዩት ልሂቃን ሲጠፉ፣ እንደ ከዋክብት የሚታዩት ክቡራን ሲረግፉ በጽናት መቆም። አብረው የነበሩ ፈርተውና ተሽጠው ሲከዱ በጽናት መቆም - ሀገር ትፈልጋለች። በሚጸኑት ዘንድ የኢትዮጵያ ትንሣኤ እጅግ ቅርብ ብቻ አይደለም። የሚታይም ነው።
ትንሣኤ ተስፋ ነው። ፈተናው እንደሚያልፍ ተስፋ ይሰጣል። ዓርብን ላየ እሑድ የሚመጣ አይመስልም ነበር። የመቃብሩን ድንጋይ ላየ የሚነሣ አይመስልም ነበር። ማኅተሙን ላየ የሚፈታ አይመስልም ነበር። ጨለማውን ላየ ብርሃን ሩቅ ይመስል ነበር። ሁሉም ግን ተገለበጠ። ታሪክን የታሪኩ ጌታ ለወጠው።
ተስፋችን በደጅ ነው። ዓርብ ላይ እሑድን እናየዋለን። ከሞት ባሻገር ሕይወትን፣ ከመቃብር አልፈንም ትንሣኤን የምንመለከት ነን። የሚጨበጥ ሕልም የጠራ ምናብ አለን። ስለዚህም ወጀብና አውሎ ነፋስ አያስደንቀንም። ዛሬ ለነገ፣ ሞት ለትንሣኤ ቦታ እንደሚለቁ የምናውቅም፣ የምናምንም ነን።
ለኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚተጉ ብዙዎች ናቸው። የሕማማቱ ጊዜ እያለፈ ነው። አሁን ዓርብ ወደ ማታ ላይ ነን። ከጸጥታው ቀን በኋላ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ይመጣል። ከሄዱት ብዙዎች ይመለሳሉ። ከተሳሳቱት ብዙዎች ያስተውላሉ። ዓርብ ዕለት በከንቱ የጮኹት ብዙዎች ያፍራሉ። ፈራጆች ይፀፀታሉ። ተገዳዳሪዎች ይበታተናሉ። የመቃብር ጠባቂዎች ይደነግጣሉ። ኢትዮጵያ ግን አይቀሬ በሆነው ትንሣኤ ትነሣለች።
ትንሣኤው ከእሥራኤል ለዓለም እንደተገለጠው ሁሉ፣ ኢትዮጵያም ለዓለም ትገለጣለች።
የትንሣኤ በዓል የሚያስተምረንም ይሄንኑ ነው።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!!
የትንሳኤ በዓል እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የሰው ልጆችን ከሃጢያት ለማንጻት ራሱን አሳልፎ በመሰጠት ወደር የማይገኝለት ፍቅሩን በመስቀል ላይ ገልፆ በሞቱ ለሰዉ ልጆች ሁሉ ምህረት ያስገኘበት እና ሞትንም ድል በመንሳት ከሞት የተነሳበት በዓል ነው።
እኛም እየሱስ ክርስቶስን በተምሳሌትነት በመከተል እርስ በርስ በመፋቀር፣ በመተሳሰብ፣ በይቅርታና ምህረት በማድረግ ከሰዉ ልጆች ጋር ሁሉ በሰላም እንድንኖር እሱ ይርዳን።
በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምህረት፣ የመተሳሰብ፣ የመርዳዳት፣ የደስታ እና አብሮነታችን የሚጠናከርበት ይሁን።
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች የትንሣኤ በዓልን ስናከብር በአብሮነት፣በወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲሁም በመተጋገዝ እና በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል፡፡
በክፍለ ከተማችን ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችንን በማገዝ በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩ በርካታ ሰው ተኮር ተግባራትን አከናውነናል በዚህ አጋጣሚ ለዚህ የተቀደሰ ተግባር ያገዙንን አካላት በሙሉ እያመሰገንኩኝ በዓሉ የሰላም፣የጤና፣የደስታ፣ የብልፅግና፣የአብሮነት እና የመልካምነት በዓል እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና በራሴ ስም እገልጻለሁ፡፡
ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !
አቶ ክፍሌ ለማ
የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተናበት ቀን ነው፡፡የትንሳኤ በዓልን ስናስብ አንዳችን ለሌላችን መተሳሰብ የኢትዮጲያነትን ባህል የሚናሳይበት ይበልጥ የሚንደጋገፍበት አብሮነታችንን የሚናጠናክርበት ነው።
በዓሉ የደስተ፣የባረከትእና የብልፅግና እንዲሆንልን እመኛለሁ
በድጋሚ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ
የቦሌ ክ/ከ /ብ/ፓ/ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ለማ
*ሞት ክርስቶስን ከሦስት ቀናት በላይ ይይዘው ዘንድ አልቻለምና ጌታችን ከሞት መንጋጋ ወጣ*
ለመላው የቦሌ ክ/ከተማ ክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም ወጣቶች
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ
ውድ የክ/ከተማችን ወጣቶች በጌታችን ስቅለት እና ትንሳኤ የቤተ መቅደስ መጋረጃ መቀደድ በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ እንደፈረሰ ሁሉ
እኛም በዓሉን ስናከብር ከዘር ከጎጥ ከትንንሽ ሃሳቦች በመራቅ ትልቋን ሃገራችንን ኢትዮጵያን በመያዝ እንዲሁም አፍሪካዊ እሳቤን በማቀንቀን በእውነተኛ እህት እና ወንድማማችነት ስሜት እንድናከብር
በቃሉ የቤትህ ቅናት በላኝ ተብሎ እንደተፃፈ እንዲሁ ክርስቶስ ተሰቅሎ ሲመለከት ቤተ መቅደሱ በተራው ስለ ክርስቶስ እንደቀና እሱም ሰላምን እንደሰጠን እኛም ለኢትዮጵያ እድገት ብልፅግና ሰላም እና አብሮነት በመቅናት የበኩላችንን እንድንወጣ
እንዲሁም ክርስቶስ ነፍሳትን ከሲኦል እና ከእስራት ነፃ እንዳወጣ ወደ ሲኦል ወርዶ ድንቅ ስራን እንደሰራ እኛም ወጣቶች በተሰማራንበት የስራ መስክ ባለን ሞያ ሁሉ ተግተን ከልባችን በመስራት ራሳችንን ህዝባችንን እና ሀገራችንን በኢኮኖሚ ካለንበት ደረጃ ከፍ ማድረግ ይገባናል።
እኛ ወጣቶች በስቅለቱ በክፉዎች ምክር ያልሄደ ተብሎ ስሙ እንደተጠራው ራሱን ሰውሮ እና ደብቆ እንደ ቆየው በጎው እና ፃድቁ ሰው ዮሴፍ ራሳችንን ልናደርግ ይገባል እሱ የአይሁድ ሸንጎ አባል እና አማካሪ ቢሆንም ክርስቶስን ለመስቀል በተማከሩበት በክፉዎች ምክር ያልሄደ በክርስቶስ ላይ በሚሳለቁት በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ ምስጉን ሰው ነበር ራሱን ሰውሮ የቆየው ይህ ሰው ደቀ መዝሙርነቱን ይፋ ያደረገበት ዕለት ግን እጅግ ከባድ ቀን ነበር ክርስቶስ በግፍ ተገርፎ በግፍ በተሰቀለበት ዕለት እኔ የእርሱ ደቀመዝሙር ነኝ ብሎ ያለፍርሃት ራሱን ገለጠ
ይህን ለማድረግ ከጌታ ጋር ለኖሩት ደቀመዝሙራት ግን አልተቻለም ነበር በዚህ ምሳሌነት እኛ ወጣቶችም ሀገራችንን ኢትዮጵያ ሊያፈርሱ ከሚሹ ሌብነት ዘረኝነት ብልሹ አሰራሮች ከፅንፈኛ አስተሳሰቦች እንዲሁም አመለካከቶች በመራቅ እና በመከላከል በክፉዎች ምክር ባለመሳተፍ ሀገር የመገንባት ሂደቱን ልናፋጥን ይገባል
በመጨረሻም አንድ ልብ ሆነው የነበሩትን ሞት እና ሰይጣንን የከፋፈላቸው ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ባለ ብዙ ቀለም ኢትዮጵያ ሀገራችን የምታከብረው የትንሳኤ በዓል በጋራ በመተጋገዝ እንድናከብር ጥሪዬን አስተላልፋለው በድጋሜ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን አደረሳቹ
ሔለን ለገሰ የቦሌ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ ኃላፊ
የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ማዕድ አጋራ ፡፡
የቦሌ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ ለአቅመ ደካማ ማዕድ ያጋራ ሲሆን፣ በማዕድ ማጋራት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ክፍሌ ለማ ባደረጉት ንግግር የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ በበዓላት ወቅት ለዝቅተኛ ማህበረሰብ ማዕድ በማጋራት አብሮነቱን በተግባር ሲያሳይ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
“ማዕድ ስናጋራ የቆየ ኢትዮጵያዊ የመረዳዳትና የአብሮነት እሴቶቻችንን አጠናክረን በማስቀጠል ነው” ያሉት የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ክፍሌ ለማ፣ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩ የተሳካ እንዲሆን እገዛ ላደረጉ ልበ ቀና ባለሀብቶችና ተቋማት እንዲሁም መርሐ ግብሩን ላስተባበሩ የክፍለ ከተማና የወረዳዎች ወጣት ክንፍ ሀላፊዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣት ክንፍ አስተባባሪ ወ/ሪት ሄለን ለገሰ በበኩላቸው በክፍለ ከተማና በአሥራ አንዱም ወረዳዎች በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ወረዳዎች አቅመ ደካማ ለሆኑ ወገኖች የማዕድ ማጋራት እንደተደረግ ገልጸዋል፣ የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎችና አመራሮች፣ ተቋማትና በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶች እንዲሁም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪዎች ለመርሐ ግብሩ መሳካት አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ሚያዚያ 11/2017
ብልፅግና ፓርቲ ሁሌም ሰው ተኮር ተግባራት መገለጫው ነው
ብልፅግና ፓርቲ ሁሌም ሰው ተኮር ተግባራት መገለጫው ነው ።
በቦሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ አማካኝነት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የታደሱ የአቅመ ደካማ የመኖሪያ ቤት ተጠናቆ በዛሬው እለት የሁሉም ወረዳ ዘርፍ አመራሮች በተገኙበት የበዓል ስጦታ በመያዝ የቤት ርክክብ ተካሂዷል ።
በመድረኩ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ሄለን ለገሰ ብልፅግና ፓርቲ
ከምስረታው ጀምሮ ለህዝብ ቃል ከገባቸው ተግባራት መሀከል አንዱ በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ላይ ያሉትን የማህበረሰብ ክፍሎችን በመለየት አንገብጋቢ የሆነውን የመኖሪያ ቤት እድሳት በማከናወን የበርካታ ዜጎች ህይወትን መለወጥ ችሏል ።
በእያንዳንዱ እርምጃው ዜጎች ህይወታቸው እንዲለወጥ በማድረግ ድህነትን እንጂ ደሀን የማይጠላ ፓርቲ መሆኑን በተጨባጭ አስመስክሯል ።
በዚህ ሂደት ውስጥ ወጣቶች በገንዘብ ፣ በጉልበት በሀሳብና ቀድሞ ደራሽ በመሆናችን ትልቅ ደስታ ይሰማናል ይህንንም በሰፊው አጠናክረን እናስቀጥላለን በማለት
ወጣቶች ሁሌም ለሀገር አለኝታና ተስፉዎች ነን ይህንንም ባለን ሙሉ ጊዜ ለማህበረሰባችን በዚህ አግባብ የመኖሪያ ቤት እድሳት እንዲሳካ ማድረግ መቻላችን ይበልጥ ለመስራት መነሳሳትን ይፈጥራል በማለት ገልፀዋል።
በተመሳሳይ የወረዳው የወጣት ክንፍ ኃላፊ ወጣት ኢተፋ ያደሳ በመልክቱ በእያንዳንዱ የብልፅግና እሳቤ መነሻነት የሚከናወኑ ተግባራት የወጣቱን ሙሉ አቅም መጠቀም አስችሏል እንዲሁም የፓርቲያችንን ቅቡልነትን ለማረጋገጥ አቅም ሆኗል እነዚህ መሰል ተግባራት በወረዳችን እንደወጣት ክንፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልፀዋል ።
ቦሌ ወጣት ክንፍ ሚያዝያ 2017
446 ቤቶች ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ተበረከተ
ዛሬ 446 ቤቶችን ገንብተን ለአቅመ ደካሞች፣ ለሀገር ባለዉለታዎች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ የከተማችን ነዋሪዎች አስተላልፈናል።
በከተማችን ከህዝብ በምንሰበስበው ገቢ ከምናከናውናቸው ታላላቅ የልማት ስራዎች ጎን ለጎን በጎ ፍቃደኛ ባለሀብቶችን እና የተለያዩ ተቋማትን በማስተባበር የአቅመ ደካሞችን ኑሮ የሚያሻሽሉ ሰዉ ተኮር ስራዎችን እየሰራን የምንገኝ ሲሆን፣ በተለይ የተገፉ እና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት እድል ያጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እምባ ሲታበስ ማየት ደስታን ይሰጠናል።
ዛሬ ካስረከብናቸዉ 446 ቤቶች ዉስጥ በቦሌ ክፍለ ከተማ ጎላጎል አካባቢ የሚገኙትን ቤቶች ግንባታ ያገዙን የገቢዎች ሚኒስቴርን፣ የጉምሩክ ኮሚሽንን እና የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንን እንዲሁም ሌሎች በጎ ፈቃደኛ ባለሃብቶች እና ተቋማትን በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባዔ በመዲናችን አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባዔ በዛሬው ዕለት በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል በመድረኩም የአዲስ አበባ ብልፅግና ወጣቶች ክንፋ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ ለመጀመሪ ጊዜ የሚካሄደው ጉባዔው ÷"የወጣቶችን አቅም፣ለበለፀገች አፍሪካ" በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በጉባዔው ከአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወጣት አመራሮችና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ወጣት ምሁራን፣ ወጣት የማህበረሰብ አንቂዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሳትፈዋል፡፡
የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባዔ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ መገለጹን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ፡፡
“ዒድ አል ፈጥር” የረመዳን ጾምን የማጠናቀቂያ በዓል ነው፡፡ ዒድ አል ፈጥር “የምስጋና፣ የበጎ አድራጎት እና የወንድማማችነት/እኅትማማችነት” በዓል ነው፡፡ ዒድ አል ፈጥር ከአንድ ወር የጾም ጊዜ በኋላ የሚመጣ በዓል ነው፡፡ ጾሙ የሰውን ድካም፣ ዐቅም ማነስ እና ልክ የሚያሳይ ነው፡፡ ፈጣሪ ካልደገፈው በቀር የሰው ልጅ ዐቅም ውሱን መሆኑን ያሳያል፡፡ ትዕቢት፣ ጥጋብ እና ክፋት በዚህ ደካማ ሰው ላይ መብቀላቸውን ለተመለከተ፣ የሰው ጠላቱ የገዛ ጠባዩ መሆኑን ይማራል፡፡ ሰው በዘመናት ውስጥ ሌሎችን ለመግዛት የታገለውን ያህል ራሱን ለመግዛት አልታገለም፡፡ ዛሬም በሀገራችን የምናየው ፈተና በዋናነት ራስን ካለመግዛት የሚመጣ ፈተና ነው፡፡ ራሱን የማይገዛ ሰው ዐቅሙን አያውቀውም፡፡ ወደ ውስጡ አያይም፡፡ ጠላቱን ከገዛ ጠባዩ ውስጥ ከመፈለግ ይልቅ፣ ጠላቱን ከጎረቤቱ ይፈልገዋል፡፡ በዚህ የተነሣ ከገዛ ወገኑ ጋር ሲቃረን ይኖራል፡፡ እንደ ረመዳን ዓይነት ወቅቶች ውስጥን ለመመልከት የሚጠቅሙ ናቸው፡፡
ውስጣቸውን የተመለከቱ ሰዎች ምስጋና ገንዘባቸው ነው፡፡ ሰው የራሱን ልክ ካላወቀ ሌላውን አያደንቅም፤ ሌላውን አያመሰግንም፡፡ የሌለውን ካልተረዳ ያለውን አያውቅም፤ አያደንቅም፡፡ የራሱ ጠላት የገዛ ጠባዩ መሆኑ ካልገባው፣ ሌላውን ወገኑን አያፈቅርም፡፡ ለዚህ ነው የጾሙ መጨረሻ፣ ዒድ አል ፈጥር የምስጋና በዓል የሆነው፡፡ ጾሙ ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ማኅበረሰብ ድረስ ራስን ገዝቶ ለመሰባሰብ ይጠቅማል፡፡ መሰባሰቡም ከስሜት የወጣ፣ ስክነትና ራስን መግዛት ያለበት ነው፡፡ ሀገራዊ ምክክራችን ይሄን ዕሴት ቢላበስ እንጠቀማለን፡፡ መነጋገሩ ብቻ አይጠቅምም፡፡ ከስሜት ወርዶ፤ በስክነት ተሞርዶ፤ ነገን ተመልክቶ - መመካከር፡፡ ያ ከሆነ እንደ ዒድ ሁሉ፣ የምክክራችን ፍጻሜው ምስጋና ይሆናል፡፡
የዒድ ሌላው ዕሴት በጎ አድራጎት ነው፡፡ ዐቅም ለሌላቸው፤ ሁኔታው ላልተሟላላቸው ወገኖች መልካምን ነገር ማድረግ፡፡ ዝምድናን፣ ዘርን ወይም እምነትን ሳይመለከቱ ሰውን በሰውነቱ ብቻ መርዳት፡፡ የጾም ምንዳዕ ሙሉ የሚሆነው በጎ አድራጎት ከተጨመረበት ነው፡፡ በጎ አድራጎት ማለት ከራስ አጉድሎ ሌላውን መሙላት ነው፡፡ እንደ ሀገር ለመቀጠልና እንደ ሕዝብ ለመተሣሠር በጎ አድራጎት እጅግ አስፈላጊ ዕሴት ነው፡፡ ራስን በሌላው ጫማ ላይ አስገብቶ ማየት፡፡ የሌላው ጉድለት ለመሙላት ሲባል የራስን ማጣት፡፡ ለምን ወገኔ ያዝናል? ለምን ወገኔ ይከፋል? ብሎ መንገብገብ፡፡
ሁላችንም የየራሳችንን ወገን ጥቅምና መብት በማስከበር ብቻ ሀገር ልንገነባ አንችልም፡፡ ትሥሥራችን ወገን ዘለል ሆኖ፣ የሌላውን ወገን ጉዳትና ፈተና መጋራት ይገባናል እንጂ፡፡ የእኔ ቤት ሲሟላ አይደለም የእርሱ ቤት የሚሟላው፡፡ የእርሱ ቤት ሲሟላ ነው የእኔ ቤት የሚሟላው፡፡ የፖለቲካ ምኅዳራችን በዚህ ነባር ዕሴታችን ላይ ካልተመሠረተ ፍትሐዊነትን እና እኩልነትን ለማስፈን እንቸገራለን፡፡
እነዚህን ሁለቱን ዕሴቶች የሚያስተሣሥረው የዒድ ዕሴት “ወንድማማችነት/እኅትማማችነት” ነው፡፡ ወንድማማችነት/ እኅትማማችነት ማለት በጋራ ዕሴቶች፣ በመተባበር እና በጋራ ግብ ላይ የተመሠረተ ወዳጅነት ነው፡፡ ይሄ ወዳጅነት በሥነ ምግባር የተገራ፣ ፍቅርንና አንዱ ለሌላው መቆምን መሠረት ያደርጋል፡፡ የጋራ ኃላፊነትን ይወስዳል፡፡ በሀገራችን የፖለቲካ ሕይወት እጅግ አስፈላጊው/ግን እጅግ የተረሳው ዕሴት ነው፡፡ መብትንም ሆነ ግዴታን በወንድማማችነት/እኅትማማችነት መነጽር መመልከት ነገሩን ለሰውነት ቅርብ ያደርገዋል፡፡ ለእኔ ከሚለው አውጥቶ ለእኛ፤ ለእኛ ከሚለውም ጭምር አውጥቶ “ለእነርሱ እና ለእኛ”፤ ለእነርሱ እና ለእኛ ከሚለውም አውጦቶ “ለእኛ ይቅርብን፤ ለእነርሱ ይደረግ “ወደሚለው የላቀ ሰብእና ያደርሰዋል፡፡
በእምነቶች፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በማኅበረሰቦች እና በልሂቃን መካከል የተሻለውን አብሮነት የሚፈጠረው ወንድማማችነት/እኅትማማችነት ነው፡፡ የተሻለ መረዳዳት፣ የተሻለ መተዋወቅ እና የተሻለ መግባባት ይፈጥራል፡፡ ለሌላው ሲል መተዉን፤ ለሌላው ሲል መቀበልን እና ለሌላው ሲል ለበደሎች ዕውቅና መስጠትን የሚያስገኘው ዕሴት - ወንድማማችነት/እኅትማማችነት ነው፡፡ የዒድ በዓል አንዱ ዕሴት የሆነውም በዚህ የተነሣ ነው፡፡ የዒድን በዓል እነዚህን የበዓሉ ዕሴቶች እያሰብን፣ እያዳበርንና ለሀገር ግንባታ እየተጠቀም እንድናከበረው ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ ቤተሰቦች፣ ጎረቤታሞች፣ ማኅበረሰቦች እና የእምነት አባቶች ሲሰባሰቡ እነዚህ ሦስት የዒድ ዕሴቶች ጎልተው እንዲወጡና ማኅበረሰባችን እንዲገነባባቸው እንዲያደርጉ አደራ እላለሁ፡፡
ኢድ ሙባረክ!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መጋቢት 20፣ 2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
የከንቲባ አዳነች አቤቤ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት...!!
መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛ የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ኢድ ሙባረክ!!
የኢድ አል-ፈጥር በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና በረመዳን የጾም ወር የነበረ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የአንድነት የሚጠናከርበት በአል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
በድጋሚ ኢድ ሙባረክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!!
"ሰው ተኮር ተግባሮቻችን ለአብሮነታችን!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአቅመ ደካሞች የአፍጢር መርሃ ግብር ባደረጉበት ወቅት ሁለት እጆቹን በአደጋ ምክንያት በማጣቱ ምክንያት መመገብ እንኳን የማይችለው እና የ3 ልጆች አባት የሆነው አቶ አባስ መኮንን የመኖሪያ ቤት ችግር ላይ መሆኑ በመታወቁ ቅድሚያ እንዲሰጠው በተወሰነው ውሳኔ መሰረት በዛሬው እለት የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ቤቱን አስረክቦታል::
ድጋፍ የተደረገላቸው አቶ አባስ መኮንን በበኩላቸው ድጋፍ እንዲደረግ ላደረጉት ለከተማዋ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ድጋፉን በማመቻቸት ላስረከበው ለክ/ከተማው አስተዳደር ምስጋና አቅርበዋል።
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ... !!
ኢድ ሙባረክ!
1446ኛውን የኢድ አል-ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላቶቻችን ከአቅመ ደካሞች እና ከሀገር ባለውለታዎች ጋር ማዕድ ተጋርተናል።
በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የመተሳሰብ እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን !
አቶ ክፍሌ ለማ
እንኳን ለ1,446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ታላቁ የረመዳን ወር የእስልምና እምነት ዋነኛ አስተምህሮዎች በተግባር የሚገለጹበት ወቅት ነው። በዚህ ቅዱስ ውስጥ ሕዝበ ሙስሊሙ በፆምና በዱአ ለሰላም ሲጸልይ እንዲሁም እርስ በርስ በመደጋገፍ ሲያደርግ የነበረው መልካምነት ከረመዳን በኋላም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እያሳሰብኩ፣ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመልካምነት እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስም ለመግለጽ እወዳለሁ።
ኢድ ሙባረክ!
ዓለምጸሐይ ሺፈራው
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ታላቁ የረመዳን ወር የእስልምና እምነት የበረከት ወር ነው በዚህ ወር በፆም በጸሎት እርስ በርስ በመደጋገፍ በአብሮነት የሚታለፍበት ወር ነው።
በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት ፣ የአብሮነት እና የብልፅግና እንዲሆን እመኛለሁ ።
ኢድ ሙባረክ!
አቶ ክፍሌ ለማ
የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ሀላፊ
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 በኅብረተሰብ ተሳትፎ የሚገነቡ ፕሮጀክቶች የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡
በልዩ ልዩ የኮሙኒኬሽን አግባቦች ዙሪያ ለቦሌ ክፍለ ከተማ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጠ፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ባዘጋጀውና ለሦስት ቀናት በቆየው በዚህ ሥልጠና በአጀንዳና መልዕክት ቀረፃ፣ በፕሮግራም አዘገጃጀት፣ እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ እና ተያያዥ ርዕሶች ዙሪያ ገለፃ የተደረገ ሲሆን፣ የክፍለ ከተማና የአሥራ አንዱም ወረዳዎች የኮሙኒኬሽን እንዲሁም የፓርቲ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል እና የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው ባስተላለፉት መልዕክት ለአንድ ሀገር እድገት የሚዲያ ሚና ትልቅ ነው ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ በማፋጠን ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ እንደሚገኙ አውስተው፣ በእነዚህ ስኬቶች የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን አመልክተዋል፡፡
“የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የተሳሳቱ መረጃዎችንና አፍራሽ አጀንዳዎችን በማክሸፍና ነባራዊ ሁኔታን ለሕዝብ በማሳወቅ እንድሁም የአገልግሎት አሰጣጥን እንድፋጠን፣የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንድፈቱ፣ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ የዘርፉ አቅም በዕውቀት እንዲገነባ የቦሌ ክፍለ ከተማ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍን እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ለማ በበኩላቸው ብልጽግና ፓርቲ በ2ኛ መደበኛ ጉባኤው ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል ጠንካራ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ መገንባት አንዱ መሆኑን አውስተው፣ በዚህ ዘርፍ የቦሌ ክፍለ ከተማ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍን ለማጠናከር የተሰጠው ሥልጠና ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክተዋል፡፡
“ሚዲያ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር ማስፈን ውስጥ ሚናው የላቀ ነው” ያሉት ኃላፊው፣ የዘርፉ ባለድርሻዎች ይህንን ሚና በብቃት ለመጫወት ከሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው አክለው አሳስበዋል፡፡
የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው አመራሩና ባለሙያው በዘርፉ የተሻለ ሥራ እንዲያከናውን የበለጠ አቅም የፈጠረ መሆኑን ገልጸው፣ ከሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀት በቀጣይ ተግባራት ላይ በማዋል ዘርፉ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡
መጋቢት 7/2017
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የሕፃናትና ወጣቶች የመጫወቻ ሥፍራ ግንባታ በይፋ ተጀመረ፡፡
በወረዳው ብራስ ጋርመንት በተባለ ድርጅት አማካይነት የሚገነባውን የመጫወቻ ሥፍራ ግንባታ ያስጀመሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም ኃይሌ ባደረጉት ንግግር በከፍለ ከተማው የሚገኙ ወረዳዎች በራስ አቅም ፕሮጀክቶችን እንዲገነቡ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የተለያዩ ፕሮጀክቶች የግንባታ ሥራዎች እየተጀመሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“ፕሮጀክቶቹ በመንግሥት በጀት ከሚከናወኑት ባሻገር በኅብረተሰቡና በአጋር አካላት ተሳትፎ መከናወናቸው የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት ከፍ ያለ ሚና ይጫወታል” ያሉት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በወረዳ 4 የተጀመረው የሕፃናትና ወጣቶች የመጫወቻ ሥፍራ የወረዳውን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት በማሳደግ ረገድ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ ብራስ ጋርመንት ለፕሮጀክቱ መሳካት ላደረገው ተሳትፎ በክፍለ ከተማው አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የወረዳ 4 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሻረው ደፋሩ በበኩላቸው ወረዳው በኅብረተሰብና በልማት አጋሮች ተሳትፎ የሕፃናትና ወጣቶች የመጫወቻ ሥፍራ ለመገንባት የማስተባበር ኃላፊነቱን ሲወስድ ልማትን ለማፋጠንና የሕዝብን ተጠቃሚነት በበለጠ ለማረጋገጥ የተጀመረውን ጥረት ለማሳካት መሆኑን ገልጸው፣ ከመጫወቻ ሥፍራው በተጨማሪ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሕፃናት ማቆያ ግንባታ እንደሚጀመርና የሕፃናትና ወጣቶች የመጫወቻ ሥፍራው በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ አስታውቀዋል፡፡
መጋቢት 8/2017
የወረዳው አስተዳደር ከሕንፃ አቅራቢ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ማኅበር ጋር በመተባበር የሚያስገነባቸው ሦስት ፕሮጀክቶች የሕፃናት መጫወቻ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ እና የአልባሳት መሸጫን ያካተቱ ሲሆኑ፣ ፕሮጀክቶችን ያስጀመሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው ባደረጉት ንግግር መንግሥት የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሰው ተኮር ተግባራትን በማከናወን ለአገልግሎት በማብቃት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
“በመንግሥት በጀት ብቻ በሚከናወኑ ሥራዎች ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አይቻልም” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ በመሆኑም ኅብረተሰቡና አጋር አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸው በመግለጽ የሕንፃ አቅራቢ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ማኅበር በገርጂ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለመገንባት ላሳየው ተነሳሽነት በክፍለ ከተማው አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የወረዳ 14 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሱራፌል ባያብል በበኩላቸው ወረዳው ለነዋሪዎች ተጠቃሚነት መረጋገጥ ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር በርካታ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው፣ የሕንፃ አቅራቢ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ማኅበር ከወረዳው አስተዳደር ጋር በመተባበር የሚያስገነባቸው ፕሮጀክቶች ለአካባቢው ገጽታ መቀየር እንዲሁም ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ የወረዳው አስተዳደር የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አረጋግጠዋል፡፡
መጋቢት 9/2017
ብሔራዊነት ዘመኑን የዋጀ ፣ነገን ታሳቢ ያደረገ ገዢ ትርክት ነው!
ብልፅግና አማካኝ እሳቤን የሚያራምድ ተራማጅ ፓርቲ እንደመሆኑ ከመገፋፋት እና ከፅንፍ አስተሳሰብ ነፃ የሆነው ብሔራዊነት ገዢ ትርክት እንዲሆን ታግሎ ያታግላል።ብሔራዊነት ማለት ህገ መንግስታዊነትን መሰረት ያደረገ ኅብረብሔራዊ አንድነት ማለት ነው።
ብሔራዊነት ከዋልታ ረገጥነት እሳቤ የራቀ በመሆኑ ለአስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላማችን እንዲሁም ፍትሀዊ ዕድገታችን ትክክለኛውን ገዢ ትርክት መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል።
የሀገራችን የመተሳሰብ የመረዳዳት እና የአብሮነት ነባር እሴቶች ከፍ እንዲሉ ፓርቲያችን የጀማመራቸው ብርቱ ጥረቶችም ለሁሉም እኩል ዕድል የሚሰጥው ብሔራዊነት እንዲጎመራ ድርሻቸው ከፍ ያለ ነው።
ሲንከባለሉ የመጡ እና አዳዲስ የተፈጠሩ የነጠላ ትርክት ዕዳዎቻችን እልባት የሚያገኙት ጫፍ እና ጫፍ ቆመን በመጠላለፍ ሳይሆን የግልን እና የቡድንን ፍላጎት ለጋራ ሀገራዊ ዓላማ በማስገንዘብ በመሆኑ ሀገራዊ መግባባት ዕውን ለማድረግ ለጀመርነው ጥረትም የብሔራዊነት ገዢ ትርክትን ለመገንባት አጥብቀን መሻታችን የፓርቲያችን የጠራ አቅጣጫ ነፀብራቅ ነው።
"ለአንድ ሀገር እድገት የሚዲያ ሚና ትልቅ ነው"
ክብርት ዓለምጸሐይ ሺፈራው
የድህረ እዉነት ዘመንን የዋጀ ከመደመር እሳቤ የተቀዳ ሁሉንም አቅሞች ያሰባሰበ ኮሙኒኬሽን ለሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት ወሳኝ ነዉ!
አቶ ስዩም ከበደ
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት በብልፅግና ፓርቲ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ እና በገዥ ትርክት ግንባታ ዙሪያ ለክፍለ ከተማ እና ለወረዳ አጠቃላይ አመራር ስልጠና ሰጥቷል።
በፓርቲያችን 2ተኛው መደበኛ ጉባኤ አፅንኦት የተሰጣቸው ገዥ ትርክት እና የኮሙኒኬሽን ስራችን ዙሪያ ውጤታማ ተግባራት ለማከናወን ይረዳ ዘንድ ስልጠና መዘጋጀቱን በመክፈቻ መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል ገልፀው አመራሩ ለተግባራዊነቱ የግንባር ቀደምትነት ሚና ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የኮሙኒኬሽን እስትራቴጂው ላይ ስልጠና የሰጡት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስዩም ከበደ የብልጽግና አመራሮች የፓርቲያችንን አባላት እና መላውን ሕዝብ በማሳተፍ፣ ማኅበራዊ ሚዲያውን ለገዥ ትርክት ግንባታ፣ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ለዕውቀት ሽግግር እና የኢትዮጵያን እውነት ለመግለጥ ዘመነ መረብን የሚመጥን የኮሚኒኬሽን እስትራቴጂን የተከተለ ጠንካራ የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን ሥራ መስራት ይገባል ብለዋል።
የሚድያና ኮሙኒኬሽን ተግባራት የየዕለት ተግባር ነው ያሉት ሀላፊው የሚዲያ አጠቃቀማችንም የኮሙኒኬሽን እስትራተጂን እና መመሪያን ማዕከል ማድረግ ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።
በገዥ ትርክት ግንባታ ዙሪያ የአዲስ አበባ ብልፅግ ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ጀማል መሃመድ ስልጠና የሰጡ ሲሆን የትርክት ተረክና ታሪክ ምንነት ፣ የገዥ ትርክት፣ ብሔራዊነትና አርበኝነት በሚሉ ፅንሰ ሀሳቦች ማጠንጠኛነት ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ብዝሃነትን ማዕከል ያደረገ አሳባሳቢ ትርክት መገንባት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግና ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን ገልፀው የተዛባውን ትርክት በማከም፣ ልዩነትን በማጥበብና ስብራትን በመጠገን የብሔራዊነት ትርክት በመገንባት ሀገራዊ አንድነትን ማፅናት ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም በተሰጠው የስልጠና ርዕሶች ዙሪያ ወ/ሮ ዘይነባ ጠሃ የክ/ከተማዉ የአቅም ግንባታ ና ፓለቲካ ዘርፍ ሀላፊ እያወያዩ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽ በመስጠት እና የጋራ ተግባቦት ላይ በመድረስ ስልጠናው ተጠናቋል።
የመደመር አምዶች:-
ምሉዕ እይታ/Synoptic፦ አንድ ነገር ብቻ ነጥሎ ከመመልከት ይልቅ የነገሮችን ግንኙነትና መስተጋብር ሳይስቱ በመመልከት ለጭማሬያዊ ውጤት ይጠቁማል።
መሰናኘት/Synergy/Synchronization፦ህብረት ከንዑሳን አጠቃላይ ድምር ይበልጣል።
አስተፃምሮ/Synthesis፦መደመር የሚተጋው በስርዓት ውስጥ ተደምሮ የሚገኘው ውጤት እያንዳንዱ በግሉ ከሚያበረክተው በልጦ እንዲገኝ ነው።
ተባብሮ ኑሮ/Symbiosis፦ተደማሪዎች ምንም ጉዳት ሳያስተናግዱ የሚያተርፉበት ግንኙነት መፍጠር፣የጋራ ግብ አስቀምጦ መንቀሳቀስ።
ሥርዓት/System፦የምሉዕ እይታ፣መሰናኘት፣አስተፃምሮ፣ ተባብሮ ኑሮ እና ሚዛን መጠበቅ ድምር ውጤት ነው።
"የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማምጣት ራዕይን ለማሳካት የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ ይጠበቃል"
"የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማምጣት ራዕይን ለማሳካት የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ ይጠበቃል" ክቡር አቶ አደም ፋራህ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት
ከጥር 23 አስከ 25 በሚካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማምጣት ራዕይን ለማሳካት የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።
የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤን በማስመልከት መግለጫ የሰጡት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጉባኤውን የተሳካ ለማድረግ አብይ እና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተደራጅተው ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን እና በአሁኑ ወቅትም ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ገልጸዋል።
“ከቃል እስከ ባህል” የሚለው የጉባኤው መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ ተልዕኮን በአግባቡ የሚገልጽና ፓርቲው በጉባኤው፣ በፕሮግራሞቹ እና በምርጫ ወቅት የገባቸውን ቃሎች እና ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች በስኬት ተግባራዊ ማድረጉን እና የፓርቲውን ቀጣይ አቅጣጫ አመላካች መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ጉባኤው በሶስት ምክንያቶች ከፍተኛ ትኩረትን እንደሚስብ የገለጹት አቶ አደም ታላቅ ህዝብና ሀገርን የሚመራ ፓርቲ የሚያደርገው ጉባኤ መሆኑ አንዱ ትኩረት የሚስብበት ምክንያት ነው ብለዋል።
15 ነጥብ 7 ሚሊየን አባላት ያሉት ከአለማችን ግዙፍ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው እና በሁሉም መስኮች ስኬቶችን እያስመዘገበ የመጣው ብልጽግና ፓርቲ የሚያካሂደው ጉባኤ መሆኑ በራሱ ትኩረት እንዲሰጠው ያደርገዋል ብለዋል አቶ አደም።
በጉባኤው ፓርቲውን እና መንግስትን የሚያጠናክሩ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተቀመጠውን የፓርቲውን ራዕይ እውን ማድረግ የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይወሰናሉ ያሉት አቶ አደም ቀጣይ አቅጣጫዎችም ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል፡፡
በጉባኤው 1ሺ 700 በድምጽ የሚሳተፉ እንዲሁም ያለ ድምጽ የሚሳተፉ የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች እና የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች እንደሚሳተፉም ተገልጿል።
15 የሚደርሱ ከተለያዩ የአለም ሀገራት የእህት ፓርቲ ተወካዮችም በጉባኤው በመሳተፍ አጋርነታቸውን ያሳያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል።
በዛሬው እለት የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ ጉባዔን ለመታደም ወደ ሀገራችን ከመጡት የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ዋና ፀሀፊ ፒተር ላም ቦዝ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል።
ፓርቲያችን ያቀረበላቸውን ግብዣ በመቀበል ፓርቲያቸውንና ወንድም የሆነው የደቡብ ሱዳን ህዝብን ወክለው በጉባኤያችን ላይ በመታደማቸው ያለን አክብሮት ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ የሁለቱ ሀገራት ህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት ሊያሳድግ የሚችል ውይይት አድርገናል።
ደቡብ ሱዳን ሁሌም ቢሆን በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትሰለፍ እና ሀገራችን ኢትዮጵያ ምንጊዜም ለሚታደርግላቸው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ያላቸውን አክብሮት ገልፀውልኛል።
በቀጣይም ትብብራችንን ለማጠናከርና የሁለቱን ህዝቦች ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠናል።
Heads of Government Ethiopia
Abiy Ahmed Ali (Oromo: Abiyi Ahmed Alii; Amharic: ዐቢይ አሕመድ ዐሊ; born 15 August 1976) is an Ethiopian politician serving as the third Prime Minister of Ethiopia since 2018, and as the leader of the Prosperity Party since 2019.[1][2] He was awarded the 2019 Nobel Peace Prize “for his efforts to achieve peace and international cooperation, and in particular for his decisive initiative to resolve the border conflict with neighbouring Eritrea“..
The president of Ethiopia is the head of state of Ethiopia. The position is largely ceremonial with executive power vested in the Council of Ministers chaired by the prime minister. The current president Taye Atske Selassie Amde (Amharic: ታዬ አጽቀሥላሴ, born 13 January 1956) is an Ethiopian diplomat and politician who is serving as president of Ethiopia since 7 October 2024. He has worked as ambassador on numerous occasions in the United Nations. Prior to assuming this role, he served as the Minister of Foreign Affairs.
Adanech Abebe (Oromo: Adaanach Abeebee) is an Ethiopian politician and attorney who is serving as the thirty-second mayor of Addis Ababa since 2021. She has been serving as a deputy mayor from 2020 until 2021. She previously was the Minister of Revenue and Customs Authority from 2018[1][2] to 2020, when she became the first female to assume the role of the Federal Attorney General of Ethiopia.[3][4][5][6] She is the first woman to hold the mayorship since it was created in 1910.